ፆም_ Fasting/How do we fast/ዘወረደ
(ክፍል አንድ) ዘወረደ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደኅና ናችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን!፡፡ ልጆች! ከሰባቱ አጽዋማት መካከል ዐቢይ ጾም አንዱ እንደኾነ፣ ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት እንደኾነ፣ ጾሙ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመኾኑ ታላቅ እንደተባለ፣ ዕድሜአቸው ሰባት ዓመት ከኾናቸው ሕፃናት ጀምሮ ዅሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዐቢይ ጾምን እና ሌሎችንም አጽዋማት መጾም እንደሚገባቸው፣ እንደዚሁም ስምንቱ የዐቢይ ጾም ሳምንታት (እሑዶች) ስማቸው ማን ማን እንደሚባል ነግረናችሁ ነበር፡፡ ልጆች! ሰባቱ አጽዋማት ማን ማን እንደሚባሉም ጠይቀናችሁ ነበር አይደል? መልሱንስ ጠይቃችሁ ተረዳችሁ? በጣም ጥሩ ልጆች! መልሱን እናስታውሳችሁ፤
ስባቱ አጽዋማት የሚባሉት፡-
፩. ጾመ ነቢያት
፪. ጾመ ገሃድ (ጋድ)
፫. ጾመ ነነዌ
፬. ዐቢይ ጾም
፭. ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ)
፮. ጾመ ሐዋርያት
፯. ጾመ ፍልሰታ (የእመቤታችን ጾም) ናቸው፡፡ ዛሬ ሰኞ የዐቢይ ጾም ገብቷል። ልጆች! በዛሬው ዝግጅታችን የመጀመሪያው ሳምንት እሑድ ምን እንደሚባል እንማራለን። ትምህርቱን እንድትከታተሉት በአክብሮት ጋብዘናችኋል!
፩. ዘወረደ ልጆች!
ከዐቢይ ጾም ሳምንታት መካከል የመጀመሪያው ሳምንት <<ዘወረደ>> ይባላል፡፡ ዘወረደ ማለት ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል ሥጋ መልበሱን (ሰው መኾኑን) ያመለክታል፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወርዶ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ፣ ወንጌልን ለዓለም ካስተማረ በኋላ በፈቃዱ መከራ ተቀብሎ፣ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ከሙታን ተነሥቶ ዓለምን አድኗል፡፡ ልጆች! የመጀመሪያው ሳምንት የአምላካችን የማዳን ሥራ በስፋት የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ <<ዘወረደ>> ተብሎ ተሰይሟል፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሚቀጥለው ሳምንት ቀጣዩን ክፍል እንማራለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ: eotcmk
ፆመ ነቢያት(Christmas Fasting)
Tsom Nebiyat / Fast of the Prophets Christmas fast 11/25/2019 - 01/6/2020 Tsome Gena Hedar 15 - Tahisas 28 Sebket / Advent - The feast to commemorate the preaching of the Prophets that the Messiah will come to redeem His people from bondage. The aim of the Church is to cause her children to reflect. During the year she sets apart two seasons in which she imbues the faithful with a spirit of penitential fervor. One of these seasons, which is called Advent, from the Latin word Adventus,(arrival), embraces about five Sundays. The law and practice of the Church is observed strictly, though not so much as in Lent. It is a time for devout and penitential preparation of the soul for the proper and worthy celebration of the great feast of the Birth of Christ. In Advent (Sebket, in Amharic) a fast is kept, the Christmas Fast of 40 days beginning on 15 Hedar and ending on Christmas eve with the Fast of Gena on the 28 of Tahsas/ January 7 CHRISTMAS Year after year the Christmas season brings to the minds of all Christians the story of the Child in the manger, the shepherds on the Judean hills, the Celestial songs "Glory to God in the highest", and the Angle's message, telling that the Long expected one had come.
Liddet or Gena is the Ethiopian name for Christmas which is marked by special ceremonies. The origin is basically the same as is universally accepted. It is celebrated on 7th January (Tahsas 29 E.C) preceded by a fast of 40 days. The difference of date is due to a calendar of discrepancy since the Ethiopian calendar is based on the year of Grace 7 or 8 years after Anno Domini. The Ethiopian Christmas coincides with the date of this observance in the Eastern Orthodox dispensation. Qiddus Bale Wold is another name for Christmas in addition to Lidet or Gena. Gena is also a name for a Christmas game played by boys and grown up men (like hockey).

