Amharic Fidel ሀሁ
ልጆች ይህን የፊደል አነባበብ ተለማመዱ:-
ሀ- ግዕዝ፣
ሁ -ካዕብ፣
ሂ - ሳልስ፣
ሃ -ራብዕ፣
ሄ -ሃምስ፣
ህ -ሳድስ
ሆ -ሳብዕ

የፊደል ትምህርት ሳምንታዊ እቅድ
ሳምንት ፩:
የትምህርት ርዕስ:
፩) 2 ፊደላት (ሀ ለ)
ዝርዝር ዓላማ: በዚህ ሳምንት ልጆች ከሀ-ል ያሉትን ፊደላት ሰባቱንም ቤት ( ግዕዝ፣ ካዕብ፣ሳልስ፣ ራብዕ፣ ሃምስ፣ሳድስ እና ሳብዕ) ይማራሉ። የግዕዝ ቤትን በድምፅ/በዜማ/ እና በቅርፅ እንዲለዩ ማድረግ።
፪) ፊደላቱን ህፃናቱ( trace እንዲያደርጉ) ትልልቆቹ እንዲፅፉ ይደረጋል። ልጆቹ የፃፉትን ፊደል በስክሪኑ ላይ እንዲያሳዩ መጠየቅ።
፫) ልጆችን ለዕለቱ የተዘጋጀውን ጨዋታ የማጫወትፕሮጀክት ይኖራል።
፬) ልጆች በሀ እና ለ ቤት የሚጀምሩ የቤት እቃዎችን እንዲጠሩ ማድርግ
፭) የሰንጠረዥ ጨዋታዎችን በማዘጋጀት ትልልቆቹ ልጆች ቃላት መስራትን እንዲለማመዱ ማድረግ።
የትምህርቱ ይዘት:
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ቃላት እንዲመሰርቱ ማድረግ-
ለምሳሌ: ሀብል፣ ሀኪም፣ ለመለመ
ለትልልቆቹ:
በተመሳሳይ ቃላት ዐርፍተ ነገር እንዲሠሩ መጠየቅ-
ለምሳሌ: ሁለት መስቀል አለኝ
የዕለቱ ትምህርት ምዘና ሥልት:-
፩) ልጆች በሀ እና በ ለ ቤተሰብ የሚጀም ሩ ቃላትን እንዲናገሩ ማድረግ (የልጆቹን ስም በመጥራት መጠየቅ አልያም እርስበርስ እንዲጠያየቁ ማድረግ)
፪) ከላይ የጠሯቸውን ቃላት በወላጆች እገዛ በመፃፍና ፎቶ በማንሳት ለፊደል ክፍሉ እንዲያስገቡ የቤት ስራ መስጠት። የማስገቢያው ቀን ረቡዕ ይሆናል)
የትምህርት መርጃ መሳሪያ:
፩)ፊደላቱን የያዙ ሥዕላዊ የመማርያ ካርዶች
፪) ፊደለቱን በድምፅ ለማስተማር የሚረዱ ድረ ገፆች መጠቀም
፫) የተለያዩ የዩትዩብ ቪዲዮ መጠቀም
፬) በነጭ ሰሌዳ ላይ ፊደሎችን እየፃፉ ማስተማር።
ሳምንት ፪:
የትምህርት ርዕስ:
፩) 2 ፊደላት (ሐ መ)
ዝርዝር ዓላማ: በዚህ ሳምንት ልጆች ከሐ- መ ያሉትን ፊደላት ሰባቱንም ቤት ( ግዕዝ፣ ካዕብ፣ሳልስ፣ ራብዕ፣ ሃምስ፣ሳድስ እና ሳብዕ) ይማራሉ። የግዕዝ ቤትን በድምፅ/በዜማ/ እና በቅርፅ እንዲለዩ ማድረግ።
፪) ፊደላቱን ህፃናቱ( trace እንዲያደርጉ) ትልልቆቹ እንዲፅፉ ይደረጋል። ልጆቹ የፃፉትን ፊደል በስክሪኑ ላይ እንዲያሳዩ መጠየቅ።
፫) ልጆችን ለዕለቱ የተዘጋጀውን ጨዋታ የማጫወትፕሮጀክት ይኖራል።
፬) ልጆች በሐ እና መ ቤት የሚጀምሩ የቤት እቃዎችን እንዲጠሩ ማድርግ
፭) የሰውነት ክፍሎች
የትምህርቱ ይዘት:
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሖ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ቃላት እንዲመሰርቱ ማድረግ-
ለምሳሌ: ሐምራዊ፣ ሐረግ፣ ሕዝብ
ለትልልቆቹ:
በተመሳሳይ ቃላት ዐርፍተ ነገር እንዲሠሩ መጠየቅ-
ለምሳሌ: ሐምራዊ ቀለም እወዳለው።
የዕለቱ ትምህርት ምዘና ሥልት:-
፩) ልጆች በሐ እና በ መ ቤተሰብ የሚጀምሩ ቃላትን እንዲናገሩ ማድረግ (የልጆቹን ስም በመጥራት መጠየቅ አልያም እርስበርስ እንዲጠያየቁ ማድረግ)
፪) ከላይ የጠሯቸውን ቃላት በወላጆች እገዛ በመፃፍና ፎቶ በማንሳት ለፊደል ክፍሉ እንዲያስገቡ የቤት ስራ መስጠት። የማስገቢያው ቀን ረቡዕ ይሆናል)
የትምህርት መርጃ መሳሪያ:
፩)ፊደላቱን የያዙ ሥዕላዊ የመማርያ ካርዶች
፪) ፊደለቱን በድምፅ ለማስተማር የሚረዱ ድረ ገፆች መጠቀም
፫) የተለያዩ የዩትዩብ ቪዲዮ መጠቀም
፬) በነጭ ሰሌዳ ላይ ፊደሎችን እየፃፉ ማስተማር።
ሳምንት ፫:
የትምህርት ርዕስ:
፩) 2 ፊደላት (ሠ ረ )
ዝርዝር ዓላማ: በዚህ ሳምንት ልጆች ከሠ-ረ ያሉትን ፊደላት ሰባቱንም ቤት ( ግዕዝ፣ ካዕብ፣ሳልስ፣ ራብዕ፣ ሃምስ፣ሳድስ እና ሳብዕ) ይማራሉ። የግዕዝ ቤትን በድምፅ/በዜማ/ እና በቅርፅ እንዲለዩ ማድረግ።
፪) ፊደላቱን ህፃናቱ( trace እንዲያደርጉ) ትልልቆቹ እንዲፅፉ ይደረጋል። ልጆቹ የፃፉትን ፊደል በስክሪኑ ላይ እንዲያሳዩ መጠየቅ።
፫) ልጆችን ለዕለቱ የተዘጋጀውን ጨዋታ የማጫወት ፕሮጀክት ይኖራል።
፬) ልጆች በ ሠ እና ረ ቤት የሚጀምሩ የቤት እቃዎችን እንዲጠሩ ማድርግ
፭) የግዕዝ ቁጥሮችን ከ ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ማስተማር
የትምህርቱ ይዘት:
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
ቃላት እንዲመሰርቱ ማድረግ-
ለምሳሌ: ሠፊ፣ ሠፌድ፣ ሠራተኛ
ለትልልቆቹ:
በተመሳሳይ ቃላት ዐርፍተ ነገር እንዲሠሩ መጠየቅ-
ለምሳሌ: በላይ ቀይ ሡሪ ለብሷል።
እኔ ጠንካራ ሠራተኛ ነኝ።
የዕለቱ ትምህርት ምዘና ሥልት:-
፩) ልጆች በሠ እና በ ረ ቤተሰብ የሚጀምሩ ቃላትን እንዲናገሩ ማድረግ (የልጆቹን ስም በመጥራት መጠየቅ አልያም እርስበርስ እንዲጠያየቁ ማድረግ)
፪) ከላይ የጠሯቸውን ቃላት በወላጆች እገዛ በመፃፍና ፎቶ በማንሳት ለፊደል ክፍሉ እንዲያስገቡ የቤት ስራ መስጠት። የማስገቢያው ቀን ረቡዕ ይሆናል)
የትምህርት መርጃ መሳሪያ:
፩)ፊደላቱን የያዙ ሥዕላዊ የመማርያ ካርዶች
፪) ፊደለቱን በድምፅ ለማስተማር የሚረዱ ድረ ገፆች መጠቀም
፫) የተለያዩ የዩትዩብ ቪዲዮ መጠቀም
፬) በነጭ ሰሌዳ ላይ ፊደሎችን እየፃፉ ማስተማር።
ሳምንት ፬:
የትምህርት ርዕስ:
፩) 2 ፊደላት (ሰ ሸ)
ዝርዝር ዓላማ: በዚህ ሳምንት ልጆች ከሰ-ሸ ያሉትን ፊደላት ሰባቱንም ቤት ( ግዕዝ፣ ካዕብ፣ሳልስ፣ ራብዕ፣ ሃምስ፣ሳድስ እና ሳብዕ) ይማራሉ። የግዕዝ ቤትን በድምፅ/በዜማ/ እና በቅርፅ እንዲለዩ ማድረግ።
፪) ፊደላቱን ህፃናቱ( trace እንዲያደርጉ) ትልልቆቹ እንዲፅፉ ይደረጋል። ልጆቹ የፃፉትን ፊደል በስክሪኑ ላይ እንዲያሳዩ መጠየቅ።
፫) ልጆችን ለዕለቱ የተዘጋጀውን ጨዋታ የማጫወትፕሮጀክት ይኖራል።
፬) ልጆች በሰ እና ሸ ቤት የሚጀምሩ የቤት እቃዎችን እንዲጠሩ ማድርግ
፭) የሰንጠረዥ ጨዋታዎችን በማዘጋጀት ትልልቆቹ ልጆች ቃላት መስራትን እንዲለማመዱ ማድረግ።
የትምህርቱ ይዘት:
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ
ቃላት እንዲመሰርቱ ማድረግ-
ለምሳሌ: ሸማኔ፣ ሹራብ፣ ሰው፣ ሰጎን
ለትልልቆቹ:
በተመሳሳይ ቃላት ዐርፍተ ነገር እንዲሠሩ መጠየቅ-
ለምሳሌ: ወፍራም ሹራብ ለብሳለች።
የዕለቱ ትምህርት ምዘና ሥልት:-
፩) ልጆች በሰ እና በ ሸ ቤተሰብ የሚጀም ሩ ቃላትን እንዲናገሩ ማድረግ (የልጆቹን ስም በመጥራት መጠየቅ አልያም እርስበርስ እንዲጠያየቁ ማድረግ)
፪) ከላይ የጠሯቸውን ቃላት በወላጆች እገዛ በመፃፍና ፎቶ በማንሳት ለፊደል ክፍሉ እንዲያስገቡ የቤት ስራ መስጠት። የማስገቢያው ቀን ረቡዕ ይሆናል)
የትምህርት መርጃ መሳሪያ:
፩)ፊደላቱን የያዙ ሥዕላዊ የመማርያ ካርዶች
፪) ፊደለቱን በድምፅ ለማስተማር የሚረዱ ድረ ገፆች መጠቀም
፫) የተለያዩ የዩትዩብ ቪዲዮ መጠቀም
፬) በስነጭ ሰሌዳ ላይ ፊደሎችን እየፃፉ ማስተማር።