«ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።» ሉቃ 18:16


ከ13 የቤይ ኤርያ አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ ወጣቶችን ያሳተፈ ጉባዔ ተካሄደ

ኦክላንድ፥ ካሊፎርንያ፦ በኦክላንድ ደብረ ሰላም እየሱስ የኢ.ኦ.ተ.ቤ.  በተካሄደው የወጣቶች ጉባዔ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችና ታዳጊዎችን ያሳተፈ የወንጌልና የስነምግባር ትምህርት በቀሲስ ሠይፈሥላሴ ተሠጥቷል። ከ ኖቬምበር 8 እስከ 10 ለሶስት ቀናት የተደረገው ይህ የመጀመሪያ ጉባዔ ቀጣይነት እንዲኖረው የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ መላዕከብርሐን ባለው ለጉባዔው አዘጋጆችና ለወላጆች በአፅንኦት ጠይቀዋል።

የብዙኃን ማርያም የንግስ በዓል ላይ የታቦታተ ህጉ ዑደት እና ዝማሬ መስከረም 2012
የብዙኃን ማርያም የንግስ በዓል ላይ የታቦታተ ህጉ ዑደት እና ዝማሬ መስከረም 2012
   ስለ እንቁጣጣሽ ትርጓሜ ከሚነገሩ ታሪኮች በጥቂቱ ለማወቅ  ሊንኩን በመጫን ያንቡ
https://www.sewasew.com/p/ethiopian-new-year-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%89%81%E1%8C%A3%E1%8C%A3%E1%88%BD


በጉባዔው ላይ የተገኙት የፊደል ገበታ ክፍል ህፃናት
በጉባዔው ላይ የተገኙት የፊደል ገበታ ክፍል ህፃናት

የልጆች መንፈሳዊ ጉባዔ በሳንፍራንሲስኮ

  ሳንፍራንሲስኮ: ካሊፎርንያ-  ታላቅ የልጆች መንፈሳዊ ጉባዔ በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወኪዳነምህረት ቤተክርስትያን አዘጋጅነት በሳንፍራንሲስኮ ከተማ ተካሄደ።  

ይህ ከወትሮው በተለየ ልጆችን ያማከለ ጉባዔ ህፃናቱ አፍ በፈቱበት በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሰጠቱ የጉባዔው መልዕክት በቀላሉ ለልጆች እንዲደርስ አስችሎታል። በዚህ ጉባዔ ላይ ከደብረ ሠላም እየሱስ ቤተክርስቲያን የፊደል ገበታ ክፍል ከ 29 በላይ ህፃናትና ልጆች ተሳትፈዋል። 

በኦክላንድ ደብረ ሰላም እየሱስ ቤተክርስቲያን የህፃናት ክፍል 

የደብሩ ህፃናት ዝማሬ ሲያቀርቡ
የደብሩ ህፃናት ዝማሬ ሲያቀርቡ
© 2019 Yefidelgebeta@Iyesus church,
Powered by Webnode
Create your website for free! This website was made with Webnode. Create your own for free today! Get started